የእለቱ አበይት ዜናዎች

  • በሀማሬሳ ስደተኞች በመንግስት ወታደሮች ተገደሉ
  • በእምነታቸው ሳቢያ የታሰሩ ወንድሞቻችን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈቱ ዘንድ ጥሪ ቀረበ
  • በኬንያ ስደተኛ ኢትዬጲያውያን ለእንግልት ተዳረጉ

ሰበር ዜና:

የቄሮና የፌዴራል ፖሊስ ፍጥጫ ቀጥሏል

በአገሪቱ ዉስጥ የተጠራዉን የስራ ማቆም አድማ ተከትሎ ቄሮና ፌዴራል ፖሊስ ተፋጠዋል።የስራ ማቆም አድማው ቀጥሎ አዲስ አበባን አካሏል።

አየር ጤና፣ካራ፣ወለቴ፣ኖክ፣ጀሞና ፉሪ የንግድና የትራንስፖርት ግልጋሎት ተቋርጦ መዋሉ ታዉቋል።መንገዶች ተዘግተው ነበር።የቄሮን ትእዛዝ ተላልፈው የተከፈቱ የንግድ ድርጅታቸውን የከፈቱ ወይም መኪናን ያንቀሳቀሱ እርምጃ ተወስዶባቸውል ሲሉ ያካባቢው ነዋሪዎች ለቢቢኤን ገልጸዋል።

ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ያለምንም ቅደመ ሁናቴ ይፈቱ።ህዝብን እየጨረሰ ያለው የመከላከያ ሰራዊት ወደ ካምፕ፡ይግባ የህዝባዊ እምቢተኝነቱ ተሳታፊዎች ጥያቄ ነው።

ከፍተኛ ተኩስ ተሰምቷል።ጉዳት ሰለምኖሩ የታወቀ ነገር የለም።ፍጥጫው እንደቀጠለ ነው።ቢቢኤን ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰአታት በኋል ይለቃል።